ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ሁለት ተጫማሪ ሚሳዬሎችን ሞከረች

  • ቪኦኤ ዜና
ፎቶ ፋይል፦ የሚሳየል ሙከራውን ሰዎች በቲቪ ሲመለከቱ።

ፎቶ ፋይል፦ የሚሳየል ሙከራውን ሰዎች በቲቪ ሲመለከቱ።

ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ማክሰኞ ሁለት ተጨማሪ የክሩዝ ሚሳዬሎችን በመተኮስ መሞከሯን የደቡብ ኮሪያ ጦር አስታወቀ፡፡

ይህ በአዲሱ የአውሮፓውያን ዓመት አምስተኛው የሚሳዬል ሙከራ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

የደቡብ ኮሪያ ጦር ለቪኦኤ በላከው መግለጫ ሙከራውን ያረጋገጠ ሲሆን ዝርዝሩ እየተጠና መሆኑን አስታውቋል፡፡ ሰሜን ኮሪያ በአዲሱ ዓመት ውስጥ ብቻ ባደረገቸው አምስት ሙከራዎች ስምንት ሚሳዬሎችን መተኮሷም ተገልጿል፡፡

እኤአ በ1950 የተካሄደውን የኮሪያ ጦርነት ስምምንት መሠረት ዩናይትድ ስቴትስ በደቡብ ኮሪያ ወደ 28ሺ ወታደሮችን አስፍራለች፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ሙከራዎቹን በማወገዝ አሳሳቢ መሆናቸውንም እየገለጸች ሲሆን በተከታታይ የእንነጋገር ጥሪዋን ስታሰማ መቆየቷም ተገልጿል፡፡