የቱኒዝያ ኣርባዕቱ የሰላም ምክክር ኣባላት የዓለሙን የሰላም ሸልማት ተጎናጸፉ።
ዋሽንግተን ዲሲ —
ቱኒዝያ ከጃዝሚን አብዮቷ በኋላ ወደ እርስ በርስ መቆራቆስ እንዳትገባ ለማድረግ በወሰዱት ፈጣን እርምጃ ወደ ምክክር የገቡት አራት አካላት ናቸው የኖቤል የሰላም ተሽላሚዎች።
ሽልማቱን በተናጠል ሳይሆን በጋራ ያሸነፉት የቱኒዝያ አጠቃላይ ሠራተኞች ማህበር፣ የሃገሪቱ የህግ ባለሞያዎች ኅብረት፣ እንዲሁም የእንዱስትሪ የንግድና ዕደ-ጥበባት ኮንፈደሬሽንና የሰብአዊ መብቶች ጥምረት ናቸው።
ከዕጩዎቹ መካከል ርዕሰ-ሊቃነ ጳጳሳት ዘካቶሊካዊያን አቡነ ፍራንሲስ፣ የጀርመን ቻንስለር አንጌላ መርከል እንዲሁም አውሮፓ ውስጥ የሚኖሩት ኤርትራዊ ካህን አባ ሙሴ ዘርአይ ይገኙበታል።
ለሙሉው ዘገባ የተያያዘውን ቪድዮ ይመልከቱ።