ማርበርግ የተሰኘው ተላላፊ በሽታ በኢኳቶሪያል ጊኒ ተከስቶ 7 ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች 20 የሚሆኑ በበሽታው የተያዙ ሰዎችም የመሞት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው ተብሏል።
ልክ እንደ ኢቦላ ሁሉ ገዳይ ነው የተባለው ተውሳክ መጀመሪያ የታየው ባለፈው ጥር ሲሆን፣ አሁን በበርካታ የአገሪቱ አካባቢዎች መዛመቱ ታውቋል።
የበሽታው በፍጥነት መተለላፍ የሚያመለክተው ሥርጭቱን ለማስቆም የሚደረገውን ጥረት መፍጨመር እንደሚያስፈልግ ነው ሲል የዓለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ቢሮ አስታውቋል።
በሽታው ከተከሰተ ወዲህ ዘጠን ሰዎች በሽታው እንዳለባቸው በምርመራ ሲረጋገጥ ከነዚህ ውስጥ አንዱ ሕይወቱ ማለፉ ሲታወቅ 20 የሚሆኑት ደግሞ በበሽታው እንደተያዙ ይጠረራል ብሏል የጤና ድርጅቱ።
ካሜሩንና ጋቦን የበሽታውን ሥርጭት ለመግታት የድንበር ቁጥጥራቸውን ማጠናከራቸው ታውቋል።