ናይጄሪያ ለአንድ ሳምንት እንዲዘገይ የተደረገውን ሀገርቀፍ ምርጫ በምትካሂድበት በነገው ዕለት የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ፀጥታ የተጠበቀ እንደሚሆን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ተናገሩ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ በመላ ሃገሪቱ በቴሌቭዢን በተላለፈ ንግግራቸው በሀገሪቱ ዙሪያ ወደሚገኙት የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች የፀጥታ ኃይሎች እንዲንቀሳቀሱ ስለተደረገ ህዝቡ ያለምንም መሸማቀቅ መንቀሳቀስ ይችላል ብለዋል።
ናይጄሪያውያን አዲስ ፕሬዚዳንት እና የምክር ቤት አባላት ለመምረጥ እየተዘጋጁ ባሉበት ባሁኑ ወቅት የፖለቲካ ውጥረቱ በማባባስ ላይ መሆኑ ይስተዋላል።