ናይጄሪያ በኒጀር ባካሄደችው የአየር ጥቃት ሰባት ህፃናት ሞቱ

  • ቪኦኤ ዜና
የኒጀር ካርታ

የኒጀር ካርታ

የናይጄሪያ ወታደራዊ ኃይል ሽፍታዎችን ኢላማ አድርጎ በደቡብባዊ ኒጀር ባካሄደው የአየር ጥቃት ሰባት ህፃናት መገደላቸውንና ሌሎች አምስት ህፃናት ደግሞ መቁሰላቸው ተገለጸ።

በናይጄሪያ አቅራቢያ የምትገኘው ማራዲ ከተማ አስተዳዳሪ የሆኑት ቻዩቡ አቡባካር አደጋው መድረሱን ለአንድ የፈረንሳይ ዜና ወኪል የገለፁ ሲሆን አራት ህፃናቱ ወዲያው ሲሞቱ ሶስቱ ወደ ሆስፒታል እየተወሰዱ ህይወታቸው ማለፉን አስረድተዋል። አደጋው የደረሰው ናይጄሪያ የአየር ጥቃቱን ስታካሂድ በፈፀመችው ስህተት መሆኑንም ገልፀዋል።

አቡባካር አክለው የናይጄሪያ ወታደራዊ አይሮፕላኖች በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ ሰዎችን በመግደልና በመጥለፍ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኛ ሽፍቶችን ለማግኘት አሰሳ እያካሄዱ መሆኑን ተናግረዋል።

በናይጄሪያ የጦር ኃይሎች ሸሽተው ያመለጡ ሽፍቶች በአብዛኛው ወደ ኒጀር በመሄድ የሚደበቁ ሲሆን ድምበር ላይ የምትገኘው የኒጀር ከተማ ጥቃት ከሚደርስባቸው ከተሞች መካከል አንዷ ናት።