ካሜሩን የግድቧን ውሃ ስትለቅ የጎርፍ አደጋ ያመጣብኛል ስትል ናይጄሪያ አስጠነቀቀች

  • ቪኦኤ ዜና

በሰሜን ምሥራቅ ናይጄሪያ ማዩዱጉሪ በተባለች ከተማ ከባድ ጎርፍ መኖሪያ ቤቶችን አጥለቅልቋል።

ናይጄሪያ አጎራባቿ ካሜሩን ከትላልቆቹ ግድቦቿ አንዱ የያዘውን ውሃ እንደምትለቅ ማስታወቋን ተከትሎ የጎርፍ መጥለቅለቅ ስጋት እንደፈጠረባት ተናገረች፡፡

ካሜሩን በቅርቡ በምዕራብ እና ማዕከላዊ አፍሪካ በጣለው ከባድ ዝናብ የተነሳ የግድቡን ውሃ መልቀቅ እንደምትጀምር ያስታወቀች ሲሆን የናይጄሪያ የውሐ ጉዳዮች መሥሪያ ቤት 11 ግዛቶች የጎርፍ መጥለቅለቅ እንደሚያሰጋቸው አመልክቷል፡፡

ይህ ያሁኑ የጎርፍ ስጋት የመጣው ቀደም ብሎም የናይጄሪያ ሰሜን ምስራቃዊ ቦርኖ ክፍለ ግዛት ግድብ ተደርምሶ ከባድ የጎርፍ መጥለቅለቅ በተጎዳበት በአሁኑ ወቅት መሆኑ ነው፡፡ ለወትሮው የዝናብ እጥረት ያለባቸው የሳህል አካባቢ ሀገሮች የሆኑት ካሜሩን፣ ቻድ፣ ማሊ እና ኒዠር በጎርፍ ተጠቅተዋል፡፡

ካሜሩን የላግዶ ግድብ የያዘውን ውሃ እየመጠነች መልቀቅ እንደምትጀምር ትላንት ማስታወቋን ናይጄሪያ ተናግራለች፡፡