በናይጄሪያ የጋራ መኖሪያ መንደር በተካሄደ አመጽ ሰማንያ ሰዎች ተገድለዋል

  • ቪኦኤ ዜና

ናይጄሪያ

ናይጄሪያ ውስጥ በሚገኝ የጋራ መኖሪያ መንደር፣ የአውሮፓውያን 2018 ዓ.ም ዋዜማ ጀምሮ በተካሄደ አመፅ፣ ሰማንያ ያህል ሰዎች መሞታቸውን፣ ፖሊስና ባለሥልጣናት አስታወቁ።

ናይጄሪያ ውስጥ በሚገኝ የጋራ መኖሪያ መንደር፣ የአውሮፓውያን 2018 ዓ.ም ዋዜማ ጀምሮ በተካሄደ አመፅ፣ ሰማንያ ያህል ሰዎች መሞታቸውን፣ ፖሊስና ባለሥልጣናት አስታወቁ።

ግጭቶቹ ባብዛኛው፣ በሙስሊሞች የቀንድ ከብት ጠባቂዎችና በክርስቲያን ገበሬዎች መካከል ሲሆን፣ መነሾውም ከእርሻ መሬት አጠቃቀም ጋር የተያያዘ እንደሆነ ተገልጧል።

ፕሬዚደንት ሙሓማዱ ቡሃሪ፣ ለአካባቢው ተጨማሪ የፖሊስ ጥበቃ ማዘዛቸውን፣ አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።

ተመሳሳይ ግጭት በአገሪቱ ማዕከላዊ ክልል መቀስቀሱም የተገለጸ ሲሆን፣ ይህ ሁኔታ ደግሞ ፕሬዚደንቱ «ኣምና መረጋጋት አመጣለሁ» ያሉትን ቃል እጥርጥሬ ውስጥ የሚከት እንደሆነም ተመልክቷል።