ኤኮዋስ በኒዠሩ ሁንታ ላይ የሚዘምት ክልላዊ ኅይል በተጠንቀቅ ሊያቆም ነው

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

በኢኳዶሩ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ግድያ የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ትናንት ሐሙስ አቡጃ ላይ የተሰበሰቡት የምዕራብ አፍሪካ ሀገሮች የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ (ኤኮዋስ) መሪዎች መፈንቅለ መንግሥት በተካሄደባት በኒዠር ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን የሚመልስ ኃይል ተደራጅቶ በተጠንቀቅ እንዲጠባበቅ ትዕዛዝ ሰጡ።

መሪዎቹ ከኒዠር የመንግሥት ግልበጣው ወዲህ ተሰባስበው ሲመክሩ የትናንቱ ሁለተኛ ጊዜያቸው መኾኑ ነው። የአስራ አንዱ የኤኮዋስ አባል ሀገሮች መሪዎች ከአራት ሰዓታት በላይ የወሰደውን ዝግ ስብሰባቸውን ሲያጠናቅቁ የመከላከያ ሚንስትሮቻቸውን ክልላዊ ተጠባባቂ ኃይል እንዲያደራጁ አዝዘዋል።

ቲመቲ ኦቢዙ ከአቡጃ ያጠናቀረው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል፤ ቆንጅት ታየ ወደ አማርኛ መልሳዋለች።