ናይጀርያ ውስጥ የተለቀቁት ከ100 በለይ የሚሆኑ በቦኮ ሐራም ተጠልፈው የነበሩ “የቹፖክ ሴቶች” ናይጀርያ ባለው አሜሪካን ዩኒቨርሲቲ በመግባት አዲስ ህይወት ጀምረዋል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ናይጀርያ ውስጥ የተለቀቁት ከ100 በለይ የሚሆኑ በቦኮ ሐራም ተጠልፈው የነበሩ “የቹፖክ ሴቶች” ናይጀርያ ባለው አሜሪካን ዩኒቨርሲቲ በመግባት አዲስ ህይወት ጀምረዋል።
የናይጀርያ መንግሥት ለወራት ያህል እንክብካቤ ሲያደርግላቸው ከቆየ በኋላ ነው ትምህርት የጀመሩት።
ልጆቹ ዮላ በተባለቸው ከተማ በሚገዝኘው ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ የተጠበቀው በመጭው ወር ነበር።
በመዲናይቱ አቡጃ በነበሩትበት የማገገሚያ ማዕከል መንግሥት የመሸኛ ግብዣ አርድጎላቸዋል። ይሁንና የቺፖክ ሴቶች ቤተሰቦች ማህበር ሊቀ መንበር ያኩቡ ነከኪ የትምህርት ጊዜ ስለተጀመረ ነው ልጆቹ አሁን የገቡት ብለዋል።