ከቦርኪና ፋሶ ጋር በሚያዋስነው የኒጀር ደቡባዊ አካባቢ አንድ ጣሊያናዊ ቄስ መጠለፋቸው ተገለፀ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ከቦርኪና ፋሶ ጋር በሚያዋስነው የኒጀር ደቡባዊ አካባቢ አንድ ጣሊያናዊ ቄስ መጠለፋቸው ተገለፀ።
ፒየር ሉዊጂ ማካሊ ሰኞ ዕለት ማታ መጠለፋቸውን የኒጀርና የጣሊኣያን መንግስታት አረጋግተዋል። ቂሱን የጠለፍኩ እኔ ነኝ ያለ ወገን እስካሁን የለም። ቄሱ ምዕራብ አፍሪካ ውስጥ በአንድ ወር ውስጥ የተጠለፉ ሁለተኛ አውሮፖዊ መሆናቸው ነው። ቄሱ የአፍሪካ ሚሲዮኖች ማኅበር ለሚባል የሮማ ካቶሊክ ሚሲዮናዊ ድርጅት በተጠለፉበት አካባቢ ለአሥራ አንድ ዓመት የሠሩ መሆናቸው ታውቋል።