በኒውዚላንድ ዕገዳው ተነሳ

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል

ኒውዚላንድ ኮሮናቫይረስን መዛመት ለከለላከል ስትል ደንግጋው ከነበው የመንቀሳቀስ ዕገዳ ዛሬ ስትወጣ አዲስ ምዕራፍ ላይ መድረሷን አስታውቃለች። አንዳንድ ት/ቤቶችና የንግድ ተቋሞች እንዲከፈቱ ተፈቅዳል።

አዲስ የኮሮናቫይረስ በሽተኞች አምስት ብቻ መሆናቸውን የሀገሪቱ መንግሥት ገልጿል። ኒውዚላንድ ውስጥ ለአንድ ወር ያክል ሰዎች ከቤታቸው እንዳይወጡና አስፈላጊ ያልሆኑት የንግድ ተቋማት ሁሉ ተዘግተው ነበር።