ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስለኒው ዮርክ ጥቃት

  • ቪኦኤ ዜና

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ ጧት በትዊተር መልዕክታቸው፣ ትናንት ማክሰኞ በኒው ዮርኩ ማንሃተን ሥምንት ሰዎችን በመኪና ገጭቶ የገደለው የኡዝቤክ አጥቂ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የገባው በዲቪ/በግሪን ካርድ/ ነው ሲሉ አስታወቁ።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ ጧት በትዊተር መልዕክታቸው፣ ትናንት ማክሰኞ በኒው ዮርኩ ማንሃተን ሥምንት ሰዎችን በመኪና ገጭቶ የገደለው የኡዝቤክ አጥቂ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የገባው በዲቪ/በግሪን ካርድ/ ነው ሲሉ አስታወቁ።

ለወደፊቶቹ አሜሪካውያን፣ በተለይም ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ዘመድ አልያም ቤተሰብ ለሌላቸው፣ በሥራ ቀጥሮ የሚያመጣቸው፣ ወይም ስደተኞች ላልሆኑ የውጪ ዜጎች፣ ብቸኛው አማራጭ ዲቪ ሎተሪ/ግሪን ካርድ/ ነው። ዕድሉን ለማግኘት የሚያስፈልገውም የሁለተኛ ደረጃ ዲፕሎማ አልያም የጥቅት ዓመታት የሥራ ልምድ ነው።

​የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ግን፣ የቪዛ መረጃ በዩናይትድ ስቴትስ ሕግ መሠረት ሁሌም ምስጢር ነው። እናም በየትኛውም ዓይነት ቪዛ ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።