ዩናይትድ ስቴትስ ሩስያ ላይ የጣለችው አዲስ ማዕቀብ ዛሬ ተግባራዊ መሆኑ ተገጠ። ማዕቀቡ፣ ሩስያ እንግሊዝ ውስጥ የነበሩትን አንድ የቀድሞ ሰላይ ሰርጌስ ክሪፖል እና ሴት ልጃቸውን ዮልያ በመመረዝ ላደረሰችው ጥቃት ምላሸ መሆኑም ታውቋል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ዩናይትድ ስቴትስ ሩስያ ላይ የጣለችው አዲስ ማዕቀብ ዛሬ ተግባራዊ መሆኑ ተገጠ። ማዕቀቡ፣ ሩስያ እንግሊዝ ውስጥ የነበሩትን አንድ የቀድሞ ሰላይ ሰርጌስ ክሪፖል እና ሴት ልጃቸውን ዮልያ በመመረዝ ላደረሰችው ጥቃት ምላሸ መሆኑም ታውቋል።
ክሬምሊን ለማዕቀቡ አጸፋውን ከመስጠቱ አስቀድሞ የተሟላ ምርመራ እንደሚያካሂድና፣ ምላሹም የሩስያን ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ እንደሚሆን አስታውቋል።
ማዕቀቡ በሁለቱ ወገኖች መካከል የሚካሄደውን ውይይት አስቸጋሪ ያደርገዋል ሲል የሩስያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀ፣ ሮይተርስ የዜና አውታር ዘግቧል።
ማዕቀቡ አንዳንድ የገንዘብ ዕርዳታንና ከሩስያ ጋር የነበረውን የጦር መሣሪያ ሽያጭ እንዲቋረጥ የሚያደርግ እንደሆነም ታውቋል።