በትግራይ “የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል” የሚለው ሪፖርት እና ይዘቶቹ

ኒው ላይንስ ኢንስቲትዩት ፎር ስትራተጂ ኤንድ ፖሊሲ

በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወቅት፣ በትግራይ ክልል ውስጥ የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸሙን ለማረጋገጥ መቻሉን፣ ኒው ላይንስ ኢንስቲትዩት ፎር ስትራተጂ ኤንድ ፖሊሲ የተባለ አንድ ተቋም ባወጣው የምርመራ ሪፖርት አስታውቋል።

Your browser doesn’t support HTML5

በትግራይ “የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል” የሚለው ሪፖርት እና ይዘቶቹ

ስለ ተቋሙ ሰነድ የአሜሪካ ድምፅ አስተያየት እንዲሰጡ ሁለት ምሁራን የጠየቀ ሲኾን፣ አንደኛው፡- የሕግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ተስፋ ሰጪ ግኝቶች እንዳሉት ሲገልጹ፤ ሌላው ግን፣ ተቋሙ፣ በሌሎች የተባሉትን ሰብስቦ ከማሳተም በቀር፣ በኢትዮጵያ የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸሙን የሚያረጋግጥ በቂ መረጃ አለማቅረቡን በመግለጽ ተችተዋል፡፡

በተቋሙ ሰነድ ውስጥ ስማቸው ከተጠቀሱት የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትም፣ አስተያየት እና ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።