በኢንዶኔዥያዋ ጃቫ እና ባሊ ደሴቶች በደረሰ ከባድ ርዕደ ምድር፣ ሦስት ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ። አደጋው፣ በአካባቢው የነበረውን የነዋሪዎች ጭንቀት ያባባሰ መሆኑም ተመልክቷል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
በኢንዶኔዥያዋ ጃቫ እና ባሊ ደሴቶች በደረሰ ከባድ ርዕደ ምድር፣ ሦስት ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ። አደጋው፣ በአካባቢው የነበረውን የነዋሪዎች ጭንቀት ያባባሰ መሆኑም ተመልክቷል።
ሦስቱ ሰዎች የሞቱት፣ በሬክተር መለኪያ 6.0 የተመዘገበውና አያሌ ውድመት ያደረሰው ርዕደ ምድሩ በደረሰባት በጃቫ ደሴት እንደሆነም ታውቋል።
ዓመታዊው የዓለም ባንክና የዓለማቀፍ የገንዘብ ድርጅት /አይኤምኤፍ/ ስብሰባዎች የሚስተናገዱባት የባሊ ደሴት ነዋሪዎች፣ ንብረቶቻቸውን አንዳንድ ቁሳቁሶችን በማውጣት ተጠምደው እንደነበርም ተገልጧል።
በባሊ ደሴት አካባቢ በተለይ ስለደረሰ አደጋ የተሰማ ነገር የለም፤ ስለ ሱናሚ የተሰጠ ማስጠንቀቂያም አልተነገረም።