ሊባኖስ የመጀመሪያ የኮሮናቫይረስ ታማሚ ይፋ አደረገች

  • ቪኦኤ ዜና

ሊባኖስ በሀገርዋ የመጀመሪያ የኮሮናቫይረስ ተጠቂ መገኘቱን ይፋ አደረገች።

የአርባ አምስት ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሴት ሲሆኑ ከኢራን የተጓዙ እንደሆኑና ሆስፒታል ውስጥ ለይቶ ማቆያ ማዕከል እንዲገቡ መደረጉን ሊባኖስ አክላ አስታውቃለች።

የመጀመሪያ የኮሮና ታማሚ መገኘታችውን ይፋ ያደረጉት የሊባኖስ የጤና ሚኒስትር ለቫይረሱ ሳይጋለጡ እንዳልቀሩ የተጠረጠሩ ሌሎች ሁለት ሰዎችንም መመርመር ጀምረናል ብለዋል።