የተመድ ሪፖርት በዓለም የአይር ሁኔታ ላይ

  • ቪኦኤ ዜና
የዓለም የአየር ግለት በውቅያኖሶች እና የምድራችንን ግግር በረዶ አካባቢዎች ላይ እያስከተለ ያለው ከባድ ጉዳት በሰብዓዊ ፍጡራን ላይ አደጋ ደቅኗል ሲል አንድ አዲስ የወጣ የ ተመድ ሪፖርት አስጠነቀቀ።

አየር ንብረት ለውጥ በይነ መንግሥታት ኮሚቴ ባወጣው ሪፖርት የአየሩ ግለት ውቅያኖሶች መሞቅ የባህር ጠለል ከፍታ መጨመር የበረዶ ንጣፎችና ክምር በረዶዎች እየሳሱ መሄድን አፋጥኑዋል። ሌሎችንም የተፈጥሮ አካባቢ ችግሮችን እየከሰተ መሆኑን ገልጿል።

በዚህ ምዕተ ዓመት ማብቂያ የባህር ጠለል ከፍታ በአንድ ሜትር ገደማ እንደሚጨምር ያስጠነቀቀው ሪፖርት ይህ የአሳዎችን ቁጥር የበረዶ መጠን ይቀንሳል። ይበልጡን የከፉ የውቅያኖስ ማዕበሎችንና እና ኤል ኒኞ የመሳሰሉ ተለዋዋጭ የአየር ሁኔታዎችን ይከስታል ብሉዋል።