በነቀምቴ የታሳሪ ቤተሰቦች አቤቱታ

የነቀምቴ እስር ቤት

የነቀምቴ እስር ቤት

ላለፉት ሦስት ወራት በነቀምቴ ኩምሳ ሞረዳ ቤተ መንግሥት ታስረው የሚገኙ ግለሰቦች እስካሁን ፍርድ ቤት አለመቅረባቸው እንዳሳሰባቸው ከቤተሰቦቻቸው መካከል አንዳንዶቹ ለቪኦኤ ገልፀዋል::

ከታሳሪዎቹ መካከልም "ምግብና ውሃ ባለማግኘታችን ለእንግልትና ለበሽታ እየተጋለጥን ነው" ብለዋል።

ትናንት ጥቂት ታሳሪዎች የተለቀቁ ሲሆን አስተያየታቸውን ግን መስጠት እንደማይፈልጉ ተናግረዋል። የከተማው ባለሥልጣናት ተጠይቀው መልስ ከመስጠት ተቆጥበዋል::

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ ከፍያለው ተፈራ ግለሰቦቹ “በምዕራብ ኦሮምያ ይንቀሳቀሳል” ካሉትና “ሽፍታ” ሲሉ ከጠሩት ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ጥርጣሬ መያዛቸውን ለቪኦኤ ገልፀዋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በነቀምቴ የታሳሪ ቤተሰቦች አቤቱታ