አዲስ አበባ —
"ኦብነግ እና ሌሎች ፓርቲዎች ራሳቸውን ከምርጫው ማግለላቸው በቀጣዩ የምርጫ ሂደት ላይ ምንም ለውጥ እያመጣም" ሲል ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
የቦርዱ የኮሙኒኬሽን አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ በሰጡት መግለጫ፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች የቀረቡ አቤቱታዎችን ለመፍታት ከአንድ ወር በፊት ቦርዱ የሚጠበቅበትን ሁሉ ማድረጉን ገልጸው፣ ባሁኑ ወቅት ኦብነግ እና ሌሎች ፓርቲዎች ራሳቸውን ከምርጫው ማግለላቸው በምርጫ ሂደቱ ላይ “የውጤትም ሆነ የአሰራር ለውጥ አያመጣም” ብለዋል፡፡
መስከረም 20 ለሚከናወነው የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ቦርዱ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የገለጹት ሶሊያና፣ በምርጫ 2013 በሁለቱም ዙሮች ድምጽ ባልተሰጠባቸው ስፍራዎች ስለሚካሔደው ምርጫ እስካሁን ውሳኔ ላይ ያለመደረሱን አመልክተዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5