ምርጫ ቦርድ ውጤት ለዛሬ አልደረሰለትም

የምርጫ ቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ

የምርጫ ቦርድ ባጋጠሙት የተለያዩ ተግዳሮቶች ምክንያት ጊዜያዊ ውጤቱን በ10 መቀናት ውስጥ ማሳወቅ እንዳልቻለ ገለጸ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅሬታዎች፣ የትራንስፖርት ችግር እና ውጤት የማረጋገጥ ሂደቶች ጊዜ መውሰዳቸው ለጊዜያዊ ውጤቱ መዘግየት ምክንያቶች ናቸው፡፡

ለተወካዮች ምክር ቤት በኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ያሸነፈባቸውን 8 የምርጫ ክልሎች እና በአማራ ክልል አብን ያሸነፈበትን አንድ የምርጫ ክልል ጊዜያዊ ውጤትም ይፋ አድርገዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል ጉጂ በሚገኘው ነገሌ የምርጫ ክልል አንድ የግል ዕጩ ስማቸው ባለመካተቱ ምክንያት ድምጽ እንዳይሰጥ ከተደረገ በኋላ ከቦርዱ እውቅና ውጭ የተሰጠው ድምጽ፣ ግለሰቡ ቅሬታቸውን በማንሳታቸው እንዲጸድቅ መወሰኑንም ወ/ሪት ብርቱካን ገልጸዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ምርጫ ቦርድ ውጤት ለዛሬ አልደረሰለትም