አዲስ አበባ —
ምርጫ ቦርድ ከሚጠብቃቸው 942 አጠቃላይ ውጤቶች መካከል እስካሁን የደረሱት 618 መሆናቸውን አስታወቀ።
ምርጫው በተካሔደባቸው 440 የምርጫ ክልሎች ለሕዝብ ተወካዮች እና ለክልል ም/ቤቶች ከሚጠበቀው አጠቃላይ 942 ውጤት ውስጥ ወደ 35 የሚሆኑት ወደ ቦርዱ ማዕከል እንዳልደረሱ የቦርዱ መረጃ ያሳያል፡፡ በ160 የምርጫ ክልሎች ላይ በፖለቲካ ፓርቲዎች አቤቱታዎች መቅረባቸውንም ቦርዱ ገልጿል፡፡
ይህን ጨምሮ ቦርዱ የሚያከናውነው የማጣራት ሂደት ውጤት በጊዜ ማሳወቅ እንዳይቻል ማድረጋቸውን የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ተናግረዋል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5