ደቡብ ሱዳን በቀንድ ከብቶች ሳቢያ በተነሳ ግጭት ወደ 70 የሚደርሱ ሰዎች ሕይወት አለፈ

ፎቶ ፋይል፦ የታጠቀ ከብት ጠባቂ ላሞቻቸውን ሲጠብቁ፤ ቶንጅ አካባቢ፣ ደቡብ ሱዳን የካቲት 16/2020

በደቡብ ሱዳን በቀንድ ከብቶች ምክንያት በተለያዩ ጎሳዎች መሃከል በተነሳ ግጭት ወደ 70 የሚደርሱ ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ባለሥልጣናት እና ምስክሮች ገለጹ፡፡ ዱክ በተሰኘው አውራጃ በነበረ ግጭት 14 ሰዎች ተገድለው ሌሎች 13 ደግሞ መቁሰላቸውን የደቡብ ሱዳን የማዕከላዊ ምስራቅ ፓንገሊ ግዛት ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡

የጆንገሊ ሃገረገዥ ቷኦንግ ማጆክ ለአሜሪካ ድምፅ ሳውዝ ሱዳን ኢን ፎከስ መሰናዶ የዱክ አውራጃ የክብቶች ማደሪያ እሳቸው አሸባሪ ሲሉ በጠሯቸው ከጎረቤት ከፓይቦር አስተዳደር በመጡ ወጣቶች ጥቃት እንደደረሰበት ገልጸዋል፡፡ ወታቶቹ ከብቶቹን በድጋሚ ሰኞ ዕለት ማማሻውን መመለሳቸው ታውቋል፡፡

እሁድ ዕለትም ከሱዳን ኦምራን ማኅበረሰብ እንደመጡ የሚታመኑ ማኅበረሰቦች ረብከና በተሰኘው አውራጃ ካለ የክብቶች ማደሪያ እንስሳቶችን የዘረፉ ሲሆን በወቅቱ በተነሳ ግጭት 7 ሰዎች ሞተው ሌሎች 10 ሰዎች ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው የግዛቱ የጸጥታ አማካሪ ስቴፋን ሳላም አስታውቀዋል፡፡ ሳላም “አረቦቹ ወጣቶች በፓያንግጋይ የሚገኘውን የከብቶች ማደሪያ ዘረፈዋል፡፡ ከወጣቶቻችን ጋር በነበረው ግጭትም ሰባት ሰዎችን ከእኛ ወገን ገድለዋል” ብለዋል፡፡

ይህ ሁኔታም በካርቱም እና ጁባ የሚገኙት የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲዎች ሁለቱም አካላት ወደ ውይይት እንዲመጡ የሚጋብዝ መግለጫ እንዲያወጡ አድርጓቸዋል፡፡