በሀገራዊ ምክክሩ የታጠቁ ኀይሎች እንዲሳተፉ እየሠራ እንደሆነ ኮሚሽኑ አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

በሀገራዊ ምክክሩ የታጠቁ ኀይሎች እንዲሳተፉ እየሠራ እንደሆነ ኮሚሽኑ አስታወቀ

በኦሮሚያ እና በዐማራ ክልሎች እየተንቀሳቀሱ ያሉ የታጠቁ ኀይሎች፣ በሀገራዊ የምክክር መድረክ እንዲሳተፉ እየሠራ እንደኾነ፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የተቋሙ ኮሚሽነር ዶ/ር ዮናስ አዳዬ፣ ከመንግሥት ጋራ እስከ ትጥቅ ግጭት ያደረሱትን ጨምሮ ማንኛውንም ልዩነት በውይይት መፍታት እንደሚገባ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ለዚኽም፣ የታጠቁትን ኀይሎች ወደ ምክክር መድረኩ ለማምጣት፣ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከአባ ገዳዎች፣ ከምሁራንና ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋራ “እየሠራን እንገኛለን” ብለዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።