የሰሜን አትላንቲክ ቃልኪዳን አገሮች ድርጅት ኔቶ፣ በአፍሪካ የጋራ ወሰኖቻቸው በሽብርተኝነት ለታወከውና ጂ ፋይቭ ለሚባሉት 5 የሳህል አገሮች የጋራ ግምባር የተጠናከረ ድጋፍ መስጠት የሚችሉበትን መንገድ እያጠና ነው፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ በቅርቡ ለጸጥታው ምክር ቤት የጻፉትን ደብዳቤ ጠቅሶ፣ አሶሼይትድ ፕሬስ እንደዘገበው፣ በተለይ ሦስቱ አገሮች ማሊ፣ ኒጀርና፣ ቡርኪና ፋሶ በድንበሮቻቸው አካባቢ በሚካሄዱ የጅሃድ ተዋጊዎች ጥቃት፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት ጠፍቶበታል፡፡
ዋና ጸሀፊው በደብዳቤያቸው፣ ኔቶ የሚያደርገው ድጋፍ ትክከለኛ መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህንን ድጋፍ የሚያጠናክርና የጂ ፋይፍ አገሮችን የሚረዳ የተባበሩት መንግሥታ ድርጅት ጽ/ቤት የመቋቋም አስፈላጊነትን የሚያምኑበት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በዚህም መሰረት፣ ከአምስቱ የማሊ፣ ሞሪቴኒያ፣ ኒጀር፣ቻድ እና ቡርኪናፋሶ አገሮች የተወጣጡ፣ 5ሺ ወታደሮች፣ በተባበሩት መንግሥታት፣ የገንዘብ ድጋፍ የሚሰጣቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ይሁን እንጂ፣ የተባበሩ መንግሥታት ትልቁ የፋይናንስ ለጋሽ የሆነቸው ዩናይትድ ስቴትስ ፣በፈረንሳይና በርካታ አገሮች ድጋፍ የቀረበውን ይህን እቅድ ተቃውማለች፡፡
ባለፈው ሰኔ፣ በተባበሩት መንግሥታት የዩናይትድ ስቴትት ረዳት አምባሰደር የሆኑት ጄፍሪ ደሎረንትስ፣ ሽብረተኝነትን በመዋጋትና ሰላምን በማስፈኑ ሂደት፣ የተባበሩት መንግሥታትን ገለልተኝነት አስመልከቶ የጠራ መስመር ማየት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡
ዩናትይድ ስቴትስ ለዓመታት ለሳህል አገሮች የምትሰጠውን እርዳታ በተባበሩት መንግሥታት በኩል ሳይሆን በቀጥታ ማድረግ እንደምትፈልግ ስታስታውቅ ኖራለች፡፡