ኔቶ ለሩሲያ የሚሳይል ጥቃት አፀፋዊ ዕርምጃ ሊወስድ ነው

  • ቪኦኤ ዜና

የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን አገሮች ድርጅት/ኔቶ/ ዋና ጸሐፊው ጄንስ ስቶልንበርግ

የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን አገሮች ድርጅት/ኔቶ/ ወታደራዊ ሕብረት፣ ለሩስያ የሚሳይል ጥቃት አፀፋዊ ዕርምጃ እንደሚወስዱ፣ ዋና ጸሐፊው ጄንስ ስቶልንበርግ አስታወቁ።

ዋና ጸሐፊው ይህን ዛሬ ሲያስታውቁ፣ ቀደም ያለውን ዓለማቀፍ የረዥም ርቀት ጦር መሣሪያ ውል ሩስያ እንድታከብር አሳስበዋል። የድርጅቱ ወታደራዊ ሕብረት አባሎች እንዳስገነዘቡት፣ ሞስኮ /Novator 9M729/ ብላ የሰየመችውን አዲስ ሚሳይል ሩስያ ገንብታለች።

“ዓለማቀፉ የሚሳይል ውል በሩስያ ተጥሷል” የምትለው ዩናይትድ ስቴትስም ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ከሥምምነቱ ለመውጣት የሥድስት ወር ሂደቱን እንደጀመረች ታውቋል።

ሩስያ የገነባችው ይህ አዲስ ሚሳይል፤ አውሮፓን በድንገትም ይሁን በማስጠንቂቂያ ለማጥቃት ዕድል እንደሚሰጣት ነው ዩናይትድ ስቴትስ የምትገልፀው።