በኮቪድ ምክንያት ከመርከብ መውረድ ያልቻሉ ሠራተኞች ተማፅኖ አሰሙ

  • ቪኦኤ ዜና
ፎቶ ፋይል

ፎቶ ፋይል

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በዓለም ዙሪያ ኮሮናቫይረስን ለመከላከል በየሃገሩ በተወሰዱት ዕርምጃዎች ምክንያት፤ ለረጅም ጊዜ ከባህር ላይ ለመውረድ ያልቻሉ ከሦስት መቶ ሽህ በላይ የንግድ መርከብ ሰራተኞችን ለመርዳት እየሞከረ ነው።

በዚህ ሁኔታ ባህር ላይ ያለ አንድ የንግድ መርከብ ካፒቴን የመንግሥታቱ ድርጅት ባሰባሰበው ውይይት ላይ ተማጽኖውን አሰምቷል።

የመርከብ ድርጅቶች ዋና ሥራ አስፈፃሚዎችንና የሃገሮች የትራንስፖርት ባለሥልጣናት ባሰባሰበው ውይይት ላይ ባሰማው ተማጽኖ ከአንድ ዓመት በላይ ከባህር ላይ ያልወረዱ መርከበኞች መኖራቸውን ገልጿል።