የጋቦን ወታደራዊ መንግሥት “ወደ ሲቪላዊ አስተዳደር የሚያሸጋግር አካታች ብሔራዊ ምክክር’ ሲል በገለጸው ጉባኤ ላይ ለመታደም፣ በሺሕዎች የተቆጠሩ ሰዎች ወደ ዋና ከተማዋ ሊብረቪል መግባት ጀምረዋል፡፡
ከአሁን ቀደም ወታደራዊው ገዢ ጄኔራል ብራይስ ክሎይቴር ኦሊጉዊ ንጉዌማ፣ “እአአ በሚቀጥለው 2025 በነሐሴ ወር ሥልጣን ለሲቪላዊ አስተዳደር አስረክባለሁ፤” ብለው ነበር፡፡ ተቃዋሚ ቡድኖች በበኩላቸው፣ ወታደራዊ ገዥዎቹ፥ ምክክሩን ሥልጣን ላይ የመቆያ ዘዴ ሊያደርጉት አይገባም፤ ሲሉ አሳስበዋል፡፡
በሞኪ ኤድዊን ኪንዴዜጋ ከአጎራባችዋ ካሜሩን የተጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።