ባንክ ለማቋቋም 5 ቢሊዮን ብር - የኢኮኖሚና ፖለቲካዊ አንድምታው

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ አገልግሎት ላይ ያሉትን ባንኮች ጨምሮ፣ አዳዲስ የሚመሰረቱት ባንኮች፣ የተከፈለ አነስተኛ ካፒታላቸው ከ500 ሚሊዮን ወደ 5 ቢሊዮን ብር ከፍ እንዲል፣ በቅርቡ ባወጣው መመሪያ ወስኗል፡፡ ከመጋቢት 4 ቀን 2013 ጀምሮ፣ ተፈጻሚ ሆኗል የተባለው መመሪያ፣ ባንኮች ተዋህደው ካፒታላቸውን እንዲያሳድጉ ወይም እንዲፈርሱ የሚያስገድድ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የባንክ ባለሥልጣን፣ ለአሜሪካ ድምጽ እንደተናገሩት፣ መጭዎቹ ትናንሽና አዳዲሶቹ ባንኮች ቀርቶ፣ አሁን ያሉት አብዛኞቹ ባንኮች፣ የማበደር አቅማቸው ደካማ በመሆኑ የባንኮችን አቅም ማጎልበት አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

የኢኮኖሚ ባለሙያውና መምህር ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገዳ ደግሞ፣ ውሳኔውን እጅግ በጣም የሚደግፉት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እሳቸው የሚደግፉበት መንገድ ግን የተለየ፣ ከኢኮኖሚው ይልቅ ፖለቲካዊ አንድምታና ጠቀሜታ ያለው መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ “ባንኮች በዘውግ እና ሀይማኖት መደራጀት የለባቸውም ይላሉ፡፡ ይህ "ስር የሰደደ አደጋ(እሳቸው እንደሚሉት systemic risk) ያመጣል፡፡"

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ባንክ ለማቋቋም 5 ቢሊዮን ብር - የኢኮኖሚና ፖለቲካዊ አንድምታው