የኢትዮጵያ መንግሥት ከባንክ በሚበደረው የገንዘብ መጠንና የጊዜ ገደብ በሚመለከት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ገደብ መቀመጡ በሀገሪቱ የተከሰተውን የዋጋ ንረት ሊያረጋጋ ይችላል ሲሉ የንግድና ምጣኔ ሐብት ባለሞያዎች ተናገሩ።
Your browser doesn’t support HTML5
በ2000 ዓ/ም ተሻሽሎ እስካኹን በሥራ ላይ ያለው፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዐዋጅ፣ መንግሥት በፈለገው መጠን ገንዘብ እንዲበደር የሚፈቅድ በመኾኑ "ገንዘብ ያለገደብ ገበያ ላይ እንዲዘዋወርና የኑሮ ውድነት እንዲንር አስተዋፆ አድርጓል" የሚሉት ባለሙያዎቹ ኾኖም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት እየተደረገበት የሚገኘው፣ ረቂቅ አዋጅ መንግሥት ከባንኩ በሚወስደው ብድር ላይ የመጠን ገደብ የሚያስቀምጥ አንቀጽ መካተቱ ተገቢ ነው" ብለው ያምናሉ።