የአውሮፓ ኅብረት ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሰባት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

Your browser doesn’t support HTML5

የአውሮፓ ኅብረት ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሰባት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

የአውሮፓ ኅብረት እና የኅብረቱ አባል ሀገራት በጋራ በመኾን፣ ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ የሰባት ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አደረጉ፡፡

ኮሚሽኑ፣ ዘንድሮ፣ ከውጭ ለጋሾች ለማግኘት ከዐቀደው 12 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ አብዛኛውን እንዳሳካ፣ ዋና ኮሚሽነሩ ፕሮፌሰር መስፍን አርኣያ ተናግረዋል፡፡ ይኹን እንጂ፣ ኮሚሽኑ ለሚያከናውነው ሥራ፣ ከውጭ በሚያገኘው የገንዘብ ድጋፍ ላይ ተስፋ እንደማያደርግ ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ፣ “ኅብረቱ፣ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እና ዕርቅ እንዲመጣ፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የጀመረውን ሥራ መደገፉን ይቀጥላል፤” ብለዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።