የናሳ የጨረቃ ጉዞ መርሐ ግብር መራዘም እና የግል ድርጅቶች ተሳትፎ

Your browser doesn’t support HTML5

የናሳ የጨረቃ ጉዞ መርሐ ግብር መራዘም እና የግል ድርጅቶች ተሳትፎ

የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የኤሮኖቲክስ እና የጠፈር አስተዳደር - በምኅፃሩ ናሳ፣ ከኀምሳ ዓመታት በኋላ ሰውን ወደ ጨረቃ ለመላክ እየተዘጋጀ ነው፡፡ የጉዞ መርሐ ግብሩንም በሦስት ደረጃዎች ነድፎ እየሠራ ይገኛል።

ናሳ፣ ከአንድ ዓመት በፊት ባደረገው ተመሳሳይ የጨረቃ ጉዞ ተልዕኮውን አሳክቷል። ለዚህ ዓመት ያቀደውን ሌላ የጉዞ ዕቅድ ደግሞ አራዝሞታል።

የዩናይትድ ስቴትስ የኅዋ ጥናት አንዱ አካል የኾነው የጨረቃ ላይ ምርምር፣ አሁን በብሔራዊ የኤሮኖቲክስ እና የጠፈር አስተዳደር ተቋሙ(ናሳ) እና በግል ድርጅቶችም እንደቀጠለ ይገኛል።

በእነዚህና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡን፣ በናሳ ጆንሰን ማዕከል የአስትሮፊዚክስ ሳይንስ የኅዋ አየር ኹኔታ እና የፀሐይ ተመራማሪ የኾኑትን ዶክተር ጥላዬ ታደሰን ጋብዘናቸዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።