የናሚቢያ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት በዘንድሮው ምርጫ የመወዳደር እቅድ እንደሌላቸው ተናገሩ

  • ቪኦኤ ዜና

የናሚቢያ ፕሬዚዳንት ሃጌ ጌንጎብ ሕይወት ማለፍን ተከትሎ ሀገሪቱን በጊዜያዊነት ለመምራት ዛሬ ቃለ መሐላ የፈፀሙት ናንጎሎ ምቡምባ

የናሚቢያ ፕሬዚዳንት ሃጌ ጌንጎብ ሕይወት ማለፍን ተከትሎ ሀገሪቱን በጊዜያዊነት ለመምራት ዛሬ ቃለ መሐላ የፈፀሙት ናንጎሎ ምቡምባ በዓመቱ መጨረሻ በሚደረገው ምርጫ የመወዳደር እቅድ እንደሌላቸው ተናገሩ።

ትናንት እሁድ በሀገሪቱ ዋና ከተማ ዊንድሆክ በሚገኘ ሆስፒታል ውስጥ ያረፉትን ፕሬዚዳንት ጌንጎብን ሞት ተከትሎ ሀገሪቱን በጊዜያዊነት እንዲመሩ ሥልጣን የተሰጣቸው፤ ጌንጎብ ዛሬ ቃለ መሐላ ከፈፀሙ በኋላ፣ “አትደናገጡ በሚቀጥለው ምርጫ እዚህ አልኾንም”

ጊዜዊ ፕሬዚዳንት ሆነው የተሰየሙት ምቡምባ የተጣለባቸውን ከባድ ኃላፊነት በመግለጽ የናሚቢያን ህዝብ በእኩልነትና "በፍፁም ቁርጠኝነት" ለማገልገል ያላቸውን ዝግጁነት ገልጸዋል።

ይህ የፕሬዝዳንትነቱን ስፍራ ሊፈልጉ ይችላሉ የተባሉትና በምክትል ፕሬዚዳንት ለተሾሙት ኔቱምቦ ናንዲ-ንዴትዋህ መንገድ ሊከፍት እንደሚችል ተገምቷል፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንቷ በምርጫው ካሸነፉ ከደቡብ አፍሪካ አገሮች የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዚዳንት ያደርጋቸዋል ተብሏል፡፡

ይሁን እንጂ ከፓርቲያቸው ከደቡብ ምዕራብ አፍሪካ ህዝቦች ድርጅት (SWAPO) የውስጥ ተፎካካሪ ሊገጥማቸው እንደሚችልም ተመልክቷል፡፡

ፓርቲያቸው ናምቢያ ነጻነቷን ካገኝችበት እኤአ ከ1990 ጀምሮ ሀገሪቱን ሲያስተዳደር ቆይቷል፡፡ ሟቹ የቀደሞ ፕሬዚዳንት ጌንጎብ በቅርቡ በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት በዘር ማጥፋት የተከሰሰችው እስራኤልን ትደግፋለች ያሏት ጀርመንን ሲነቅፉ ነበር።

ጌንጎብ ጀርመን እኤአ በ1800ዎቹ በናሚቢያ በአስር ሺዎች በሚቆጠሩ አፍሪካውያን ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽማለች ብለዋል፡፡