"በሸዋሮቢት እስር ቤት ከፍተኛ የማሰቃየት ተግባር ተፈጽሞብናል" ተከሳሾች

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት

የሙስሊም ማኅበረሰብ ጥያቄዎች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ከእስር እንዲፈቱ ተንቀሳቅሳችኋል በሚል በእነከድር መሐመድ መዝገብ በሽብር አድራጎት የተከሰሱ 19 ሰዎች በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት በነበራቸው ቀጠሮ፤ በሸዋሮቢት እስር ቤት ከፍተኛ የማሰቃየት ተግባር እንደተፈፀመባቸው ለችሎት ማስረዳታቸውን ጠበቃቸውና ቤተሰብ ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ።

የሙስሊም ማኅበረሰብ ጥያቄዎች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ከእስር እንዲፈቱ ተንቀሳቅሳችኋል በሚል በእነ ከድር መሐመድ መዝገብ በሽብር አድራጎት የተከሰሱ 19 ሰዎች በዛሬው ዕለት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በነበራቸው ቀጠሮ ፤ በሸዋሮቢት እስር ቤት ውስጥ በአምስት ተከሳሾች ላይ ከፍተኛ የማሰቃየት ተግባር እንደተፈፀመባቸው አንድ ተከሳሽ አቤቱታ አቀረበ።

ጽዮን ግርማ በዛሬ ችሎት ተከሳሾቹን ወክልው ችሎት የቆሙትን ጠበቃ አቶ ሰኢድ አብደላና የአንዱን ተከሳሽ እናት አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች።

Your browser doesn’t support HTML5

"በሸዋሮቢት እስር ቤት ከፍተኛ የማሰቃየት ተግባር ተፈጽሞብናል" ተከሳሾች