የሙጋቤ አስከሬን ሃራሬ ገባ

  • ቪኦኤ ዜና
ባለፈው ሳምንት ህክምና ላይ በነበሩበት በሲንጋፖር ሆስፒታል ያረፉት የቀደሞ የዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ አስከሬን ዛሬ ሃራሬ ገብቷል።

ለሰላሳ ሰባት ዓመታት ዚምባቡዌን የገዟት ሙጋቤ ያረፉት በዘጠና አምስት ዓመታቸው ሲሆን ቅዳሜ ሃራሬ ላይ በመንግሥትዊ ደረጃ በተሰናዳ ግዙፍ ሥነ ስርዓት ስንብት ይደረግና ዕሁድ ቀብራቸው ይፈፀማል ተብሎ ይጠበቃል።

የሮበርት ሙጋቤን አስከሬን ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች በሺዎች የተቆጠሩ ለቀስተኞች በሃዘን አቀባበል እድርገዋል።

የአሁኑ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ እስከ ቀብሩ ዕለት ድረስ ብሄራዊ የሃዘን ወቅት የሚዘልቅ ማወጃቸው ይታወሳል።