ከአዲስ አበባ ከተማ እንዲሁም ከአማራ እና ከኦሮሚያ ክልሎች በቁጥጥር ሥር ከዋሉ ወራትን ያስቆጠሩ የሕዝብ እንደራሴዎች፣ እስከ አሁን ክስ ሳይቀርብባቸው በእስር እንዲቆዩ መደረጋቸው፣ የወከሉትንም ሕዝብ መብት ጥያቄ ውስጥ እንደሚያስገባ አስተያየት ሰጪዎች ተናገሩ።
የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ደ’ኤታ አቶ ታዬ ደንደኣ ባለቤት ወይዘሮ ስንታየሁ ዓለማየሁ፣ አቶ ታዬ ደንደአ ከታሰሩ ሁለት ወር ቢያልፋቸውም ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን፣ ከጠበቆቻቸው ጋራም እንዳይገናኙ መደረጋቸውን ተናግረዋል።
SEE ALSO: የአቶ ታዬ ደንዳአ ቤተሰቦች ከመኖሪያ ቤታቸው እንዲወጡ መደረጋቸውን ገለጹየኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ኅብረት ዋና ዲሬክተር አቶ ያሬድ ኀይለ ማርያም፣ መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅን በመጠቀም በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው ተጠርጣሪዎች አያያዝ ተገቢነት እንደሌለው ተችተዋል። በተለይ የሕዝብ ተወካዮች ክስ ሳይቀርብባቸው በእስር መቆየታቸው፣ “የወከሉትንም ሕዝብ መብት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ አካሔድ ነው፤” ብለዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5