ትላንት ረፋድ በሞያሌ በከሰተዉ ግጭት ስምንት ሰዎች እንደሞቱና ከአርባ በላይ እንደቆሰሉ የሞያሌ ሆስፒታል ገለፀ። በሆስፒታሉ የውስጥ ዶክተር የሆኑ ዶ/ር ንጉሱ አዱኛ እንደተናገሩት ከሞቱት ሰዎች ህፃናት እንደነበሩበት ገልፀዋል።
ትላንት ረፋድ በሞያሌ በከሰተዉ ግጭት ስምንት ሰዎች እንደሞቱና ከአርባ በላይ እንደቆሰሉ የሞያሌ ሆስፒታል ገለፀ። በሆስፒታሉ የውስጥ ዶክተር የሆኑ ዶ/ር ንጉሱ አዱኛ እንደተናገሩት ከሞቱት ሰዎች ህፃናት እንደነበሩበት ገልፀዋል።
ለመታከም ወደ ሞያሌ ከመጡ ቁጥራቸው ከአርባ በላይ ቁስለኞችም ከ13 በላይ ወደ ያቤሎ ሆስፒታል እና ሶዶ ሆስፒታል እንደተላኩም ገልፀዋል። የትላንቱ የሞያሌ ግጭት በከተማዋ አምስት የተለያዩ ቦታዎች የተከሰተ ሲሆን ዛሬ ጠዋትም አንድ ወጣት ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በተተኮሰ ጥይት መገደሉን የሞያሌ ከተማ ነዋሪዎች ለአሜርካ ድምፅ ገልፀዋል።
በቦረና ዞን የሞያሌ ወረዳ ፀጥታ ደኅንነት ኃላፊ አቶ ንጋቱ ካሳሁን የክልሉ መንግሥትና የፌደራል መንግሥት በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲያፈላልግ ጠይቀዋል፡፡
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5