በቅርቡ ሜዲቴራኒያን ባህር ሊቢያ ጠረፍ ላይ ከአንድ መቶ በላይ ፍልሰተኞች የተጫኑባት የጎማ ጀልባ ተገልብጣ መሞታቸው ተገለጠ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
በቅርቡ ሜዲቴራኒያን ባህር ሊቢያ ጠረፍ ላይ ከአንድ መቶ በላይ ፍልሰተኞች የተጫኑባት የጎማ ጀልባ ተገልብጣ መሞታቸው ተገለጠ።
ድንበር የለሽ ሀኪሞች ቡድን እንዳስታወቀው በዚህ የአውሮፓውያን መስከረም ወር መጀመሪያ ላይ በደረሰው አደጋ የሞቱት ፍልሰተኞች የሱዳን፣ ግብጽ፣ ሊቢያ፣ ማሊ፣ አልጄሪያ እና ካሜሩን ዜጎች ናቸው።