Your browser doesn’t support HTML5
“የጦር መሣሪያ ጨምሮ ወታደራዊ መሣሪያዎችን የጫነ መርከብ ሞቃዲሾ ወደብ ገብቷል” ሲሉ እማኞች ተናገሩ፡፡ የሶማሊያ መንግሥት ባለሥልጣናት ስለጉዳዩ የተናገሩት ነገር የለም፡፡ የመርከቡን ጭነት ምስል በቪዲዮ ያነሱ ነዋሪዎች ግን በማሕበራዊ መገናኛዎች አጋርተዋል፡፡ ሀውትዘር የሚባሉትን ከባድ መሣሪያዎች የሚያጓጉዙም ጭምር ያሉባቸው ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ከመርከቡ ሲወርዱ በምስሎቹ ላይ ታይተዋል፡፡