የዩናይትድ ስቴትስ የምግብና መድሃኒት አስተዳደር የጤና አማካሪዎች የሞደርና ኮቪድ 19 ማጠናከሪያ ክትባትን ትናንት ሀሙስ አጸደቁ፡፡
አማካሪዎቹ በአነስተኛ መጠን የሚሰጠው የማጠናከሪያ ክትባት፤ ለአረጋውያንና ከፍ ላሉ ሌሎች የጤንነት ችግሮች ለተጋለጡ ሰዎች እንዲሰጡ ወስነዋል፡፡ ከስድስት ወራት በፊት የፋይዘርን ክትባት የወሰዱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የፋይዘርን ማጠናከሪያ ክትባት እየወሰዱ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡
የምግብና መድሃኒት አስተዳደሩ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰንን የማጠናከሪያ ክትባትን አስመልከቶ በዛሬው እለት እንደሚነጋገርም ተነግሯል፡፡
የመጨረሻው ውሳኔ የሚቀጥለው ሳምንት የሚሰጥ፣ ክትባቱን ለመውሰድ የተፈቀደላቸው 66ሚሊዮን ሰዎችን ማስከተብ ቀዳሚው ግብ መሆኑም ተመልክቷል፡፡
በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ተጋላጮች ቁጥር 357 ሺ ደረሰ በኢትዮጵያ እስካሁን በኮቪድ 19 ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 357ሺ 550 መድረሱንና ከዚህ ውስጥ 326ሺ 735 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን የጤና ሚኒስቴር በትናንቱ መግለጫው አስታውቋል፡፡
ከትናንት በስቲያ በነበረው የ24 ሰዓታት ውስጥ፣ ለ8ሺ 235 ሰዎች በተደረገ የላቡራቶሪ ናሙና ምርመራ፣ 778 ሰዎች ለቫይረሱ የተጋለጡ ሆነው መገኘታቸውንም ሚኒስቴሩ በማህበራዊ ድረገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡