የሮበርት ሙጋቤ የ37 ዓመታት አስተዳደር ዘመን ሲያከትም ዚምባብዌ ዛሬ አዲስ ፕሬዚዳንት አግኝታለች።
ዚምባብዌያዊያን ከእንግዲህ ጉዳዮቻቸውንና ችግሮቻቸውን ወደ ጎን የማይገፋ መሪያቸውን የሚሰይሙበትን አዲስ ምርጫ የማድረግም ፍላጎት እንዳላቸው እየተሰማ ነው።
የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ልክ የዛሬ ሦስት ሣምንት ያባረሯቸው የያኔው ምክትል ኤመርሰን ምናንጋግዋ ከስደት ተጠርተው ዛሬ ሃራሬ ላይ ቃለ-መሃላ ፈፅመው መንበረ ርዕሰ-ብሄሩን መቆጣጠራቸው በሮበርት ሙጋቤ የ37 ዓመታት ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ በተከተተበት ሣጥን ክዳን ላይ የመጨረሻውን ሚስማር የመታ ሆኗል።
ቃለ-መሃላ ፈፅመው የዚምባብዌን ዕጣ ፈንታ የተረከቡት አዲሱ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ስድሣ ሺህ ሰው በሚይዘው የሃራሬው ብሄራዊ ስታዲየም ለተሰበሰበ ሰው ባደረጉት ንግግር “የአዲስ ዴሞክራሲ ጅማሮ ዕለት” ብለውታል።
ዚምባቤያዊያን በመጭዎቹ ስምንትና ዘጠኝ ወራት ውስጥ ከሐምሌ 15 እስከ ነኀሴ 16/2010 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ ሕገ-መንግሥታቸው በሚያዝዘው መሠረት ምርጫ እንዲካሄድ ይጠብቃሉ።
ያኔም “ሕዝቡን የሚሰማና ችግሮቹን ለመፍታት የሚሠራ መሪ እንመርጣለን” ብለው እየተናገሩ ናቸው።
ለተጨማሪና ትንታኔዎችን ለያዘው ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5