በቴክሳስ ከባድ ቅዝቃዜና በረዶ ነዋሪዎች እየተቸገሩ ነው

  • ቪኦኤ ዜና

በዩናይትድ ስቴትስ በርካታ አካባቢዎች የሰሞኑ ከባድ ቅዝቃዜ እና በረዶሟ የአየር ሁኔታ በሚሊዮኖች የተቆጠሩ ነዋሪዎችን ችግር ላይ መጣሉን ቀጥሏል። በደቡባዊቱ ቴክሳስ ክፍለ ግዛት ብዛት ያላቸው ነዋሪዎች ኤሌክትሪክ ካጡ ቀናት ተቆጥሯል።

የቴክሳስ ሃገረ ገዢ ግሬግ አበት እና የግዛቲቱን አብዛኛውን የኤለሌክትሪክ አቅርቦት የሚቆጣጠረው የህብረት ሥራ ድርጅት ኃላፊ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ያለውን የኤለሌክትሪክ ሃይል ለማጠናከር የተደረገው ጥረት ውጤት አምጥቷል ብለዋል። ካሁን በኋላ ነዋሪዎች በዙር በዙር ከሚደርሳቸው የኤለክትሪክ መቋረጥ በስተቀር በቅርቡ ሙሉ አገልግሎት እንደሚያገኙ ተስፋ አለን ብለዋል።

የቧንቧዋ ውሃ መስመሮች ላይ በደረሰ ጉዳት ምክንያትም ሰባት ሚሊዮን የቴክሳስ ነዋሪ ውሃ እያፈላ እንዲጠጣ የአስተዳደሩ ባለሥልጣናት አዘዋል።