የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ግድያ ክትትል እየተደረገበት እንደኾነ ጽ/ቤቱ አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ግድያ ክትትል እየተደረገበት እንደኾነ ጽ/ቤቱ አስታወቀ

- ቋሚ ሲኖዶስ ለምእመናንና ለተቋማቱ መንግሥት የደኅንነት ዋስትና እንዲሰጥ ጠየቀ

ባለፈው ሳምንት እሑድ ማለዳ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ በነበሩት በኩረ ትጉሃን ዘርዐ ዳዊት ኃይሉ ላይ፣ በጎንደር ከተማ ግድያ የፈጸሙ ተጠርጣሪዎችን ለማግኘት መንግሥት እየሠራ እንደሚገኝ፣ የሀገረ ሰብከቱ ጽ/ቤት ሲያስታውቅ፤ ቋሚ ሲኖዶስም፣ በምእመናንና በተቋማት ላይ እየተባባሱ ካሉ ጥቃቶች መንግሥት የደኅንነት ዋስትና እንዲሰጥ ጠይቋል፡፡

የሀገረ ስብከቱ ጸሐፊ በኵረ ሥዩማን ዐይንሸት ሞገስ፣ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ ዋና ሥራ አስኪያጁ የተገደሉት፣ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ወደ እንፍራንዝ ለመሔድ በጽ/ቤቱ በር ላይ ቆመው በነበሩበት “ያልታወቁ ሰዎች” ሲሉ በገለጿቸው ግለሰቦች ተኩስ ነው፡፡

በሌላ በኩል፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ቋሚ ሲኖዶስ፣ ትላንት ሰኞ በሰጠው መግለጫ፣ በቅርቡ፣ ከ60 በላይ አገልጋዮች እና ምዕምናን እንደተገደሉበት አስታውቋል፡፡

በንጹሐን ምእመናንና ተቋማቷ ላይ ያተኮሩ ጥቃቶች፣ “በሰማይም በምድርም ያስጠይቃሉ” ያለው ቋሚ ሲኖዶሱ፣ በአስቸኳይ እንዲቆሙና መንግሥትም የደኅንነት ዋስትና እንዲሰጥ ጠይቋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።