የመከላከያ ኀይሉ በሀገር ውስጥ ግጭቶች ድሮን መጠቀሙን እንደሚቀጥል አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

የመከላከያ ኀይሉ በሀገር ውስጥ ግጭቶች ድሮን መጠቀሙን እንደሚቀጥል አስታወቀ

በዐማራ ክልል፣ ከፋኖ ታጣቂዎች ጋራ እየተካሔደ በሚገኘው ግጭት፣ የመከላከያ ኀይሉ ሰው አልባ ተዋጊ አውሮፕላኖችን/ድሮን/ እየተጠቀመ እንደኾነ፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አረጋግጠዋል፡፡

ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ፣ ከአንድ የሀገር ውስጥ ብዙኀን መገናኛ ጋራ ባደረጉት ቆይታ፣ “የጽንፈኛውን ስብስብ ስናገኝ በድሮን መምታታችንን እንቀጥላለን፤ መሣሪያ አንመርጥለትም፤” ብለዋል፡፡

በድሮን ጥቃቶች ሰላማዊ ሰዎች እየተገደሉ እንደኾነ፣ የዐይን እማኞች እና የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች እየገለጹ ሲኾኑ፣ ፊልድ ማርሻሉ በበኩላቸው፣ “ለሕዝቡ ጥንቃቄ እያደረግን ነው፤” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋራ፣ ሦስተኛ ዙር ድርድር ሊኖር እንደሚችል የጠቆሙት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ፣ ይህም የመጨረሻው ሊኾን እንደሚችልም ገልጸዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።