ሶማልያ ውስጥ በነውጠኞች ጥቃት ቢያንስ 22 ሰዎች ተገደሉ

  • ቪኦኤ ዜና
ሶማልያ ውስጥ ነውጠኞች ዛሬ ሰኞ ባካሄዷቸው ሁለት የተለያዩ ጥቃቶች፣ ቢያንስ 22 ሰዎች መገደላቸውን፣ የዐይን ምስክሮችና ባለሥልጣናት አስታወቁ።

ሶማልያ ውስጥ ነውጠኞች ዛሬ ሰኞ ባካሄዷቸው ሁለት የተለያዩ ጥቃቶች፣ ቢያንስ 22 ሰዎች መገደላቸውን፣ የዐይን ምስክሮችና ባለሥልጣናት አስታወቁ።

የአል፡ሻባብ ነውጠኞች በማዕከላዊዋ የሶማልያ ጋለከዬ ከተማ ውስጥ በሚገኘው በአንድ አወዛጋቢ የሃይማኖት መሪ ቅጥር ግቢ ባካሄዱት የመጀመሪያው ጥቃት፣ የሃይማኖት መሪውና 10 ሰዎች ተገድለዋል።

የዐይን ምስሮች በተናገሩት ቃል፣ አንዲት ቦምብ የተጠመደባት መክና የሃይማኖት መሪውን ግቢ ጥሳ እንደገባች፣ ነውጠኞቹ ግቢውን መውረራቸው ታውቋል።

ጥቃቱ የተካሄደበት ግቢ፣ የሱፊ ሃይማኖት መሪው የሼኪ አብዲ ዌሊ ዓሊ ኤልሚ መኖሪያ እንደሆነም ተገልጧል።