የበዙት አፍሪካዊያን የሆኑ ፍልሰተኞችን ያሳፈረች መርከብ ዛሬ ስፔን ወደብ ላይ ተጠግታለች።
ዋሺንግተን ዲሲ —
የበዙት አፍሪካዊያን የሆኑ ፍልሰተኞችን ያሳፈረች መርከብ ዛሬ ስፔን ወደብ ላይ ተጠግታለች።
መርከቢቱን ስፔን ያስጠጋቻት ጣልያንና ማልታን ጨምሮ ብዙ የአውሮፓ ሃገሮች ፍልሰተኞቹን እንደማያስተናግዱ ካሳወቁ በኋላ ነው።
ባለፈው ታኅሣስ 12 ከሊብያ ዳርቻ የተነሱትን ፍልሰተኞች ሜዲቴራኒያን ባሕር ላይ ደርሰው ያጀቧቸው “የተዘረጉ ክንዶች” የሚባል የረድዔት ድርጅት ባልደረቦች ናቸው።
መርከቢቱ ላይ የነበሩት 310 ፍልሰተኞች ስፔን ወደብ እንደደረሱ ወደ ሕክምና ተቋማት ተወስደዋል።
ከተዘረጉ እጆች ውጭ ያሉ ሌሎችም ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ድንኳኖችን በማቅረብና በመትከል እያገዙ መሆናቸው ታገልጿል።