ሁለት ነዳጅ ዘይት ተሸካሚ መርከቦች በአማን ባህረ ሰላጤ ጥቃት ተፈፀመባቸው

  • ቪኦኤ ዜና
ሁለት ነዳጅ ዘይት ተሸካሚ መርከቦች ዛሬ በአማን ባህረ ሰላጤ ላይ በተፈፀመባቸው ጥቃት ጉዳት ደርሶባቸዋል። በኢራን ጠረፍ ስትራቴጃዊ በሆነው የባህር መስመር ላይ የደረሰው ጥቃት በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና ያለውን ውጥረት ያባብሳል ተብሏል።

የኖርዌ የባህር ጉዳይ ባለሥልጣን በገልፀው መሰረት ባለቤትነቱ የኖርዌ በሆነው መርከብ ሦስት ፍንዳታዎች እንደነበሩ ተገልጿል። ይህ የሆነው መደብሩ ጀርመን በሆነው የሀምበርግ መርከብ ኮኩካ ከሬጄዮስ ላይ በጥቃት የሚጠረጠር ድርጊት ከደረሰ በኋላ ነው።

መሰረቱ ባሕሬን የሆነው የዩናይትድ ስቴትስ የባህር ኃይል አምስተኛ ዘርፍ ከሁለቱም መርከቦች በአንድ ሠዓት ልዩነት የአደጋ ምልክት ከደረሰው በኋላ እየረዳቸው መሆኑን ገልጿል።

የዋይት ሃውስ ቤተ መንግሥት ቃል አቀባይ ሴራ ሳንደርስ ባወጡት መግለጫ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ፕረምፕ ስለጉዳዩ ተነግሯቸዋል። ሁኔታውን ማጤኑን ይቀጥላሉ ብለዋል።

የኢራን የባህር ኃይል ጉዳት ከደረሰባቸው መርከቦች 44 ሰራተኞችን ማትረፉን ሁለቱ መርከቦች የእሳት ቃጠሎ እንደገጣማው ኢራና የተባለው የኢራን የዜና አገልግሎት ዘግቧል።

መርከቦቹ በምን አይነት መሳርያ እንደተመቱ እስካሁን ባለው ጊዜ የተገለፀ ነገር የለም።