ሚሸል ኦባማ ከናይጀሪያ ሴቶች ጋር እንደሚቆሙ አስታወቁ

  • ቪኦኤ ዜና

ልጆቻችንን መልሱ - ሚሼል ኦባማ /ዋይት ሃውስ/


ደቡብ አፍሪካዊያን ለናይጀሪያዊያን ድጋፍ ወጥተዋል /ጆሃንስበርግ - ሐሙስ፤ ሚያዝያ 30/14/

Your browser doesn’t support HTML5

ሚሸል ኦባማ ከናይጀሪያ ሴቶች ጋር እንደሚቆሙ አስታወቁ


ናይጀሪያ ውስጥ ቦኮ ሃራም በሚባለው ፅንፈኛ ቡድን የተጠለፉ ወደ 300 የሚጠጉ ልጃገረዶችን ለመፈለግ ለሚደረገው ዓለምአቀፍ ጥረት ድጋፍ ለመስጠት የዩናይትድ ስቴትስ ቀዳሚት እመቤት ሚሼል ኦባማ ሃሽታግ ብሪንግ ባክ አወር ገርልስ (#BringBackOurGirls) - ልጆቻችንን መልሱ የሚል መልዕክት ይዘው የተነሱትን ፎቶግራፍ ትናንት በትዊተር ለቅቀዋል፡፡

የናይጀሪያ ሴቶች የሴቶች መብቶች ጉዳይ ነው ብለው በሚያምኑት በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ ሚስ ኦባማ ያደረጉትና ከጎናቸውም መቆማቸው ልባቸውን የነካው መሆኑን እየገለፁ ነው፡፡

አንዳንድ የፀጥታ ተንታኞች ደግሞ የዩናይትድ ስቴትስ በጉዳዩ ውስጥ መግባት ከሚኖረው ፋይዳ ይልቅ ጉዳቱ ሊያይል ይችላል የሚል ሥጋት እያሰሙ ነው፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡