ሜክሲኮ ላይ በደረሰው ከባድ ርዕደ ምድር ምክንያት በተደረመሱ ህንፃዎች ውስጥ የተቀበሩ ስዎችን ፍለጋ የመድህን ሰራተኞች ዛሬም ደፈ ቀና እያሉ ናቸው።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ሜክሲኮ ላይ በደረሰው ከባድ ርዕደ ምድር ምክንያት በተደረመሱ ህንፃዎች ውስጥ የተቀበሩ ስዎችን ፍለጋ የመድህን ሰራተኞች ዛሬም ደፈ ቀና እያሉ ናቸው።
በርዕደ ምድሩ አደጋ እስካሁን ባለው ጊዜ ከ2መቶ 30 በላይ ሰዎች አልቀዋል።
ትላንት በአንድ ትምህርት ቤት ላይ በተደረገ ፍለጋ የመድኅን ሰራተኞች በስብርባሪዎች ውስጥ የተቀበረች ልጅን አይተው በህይወት ያለች መሆንዋን ለማወቅ እጅዋን እንድታንቀሳቀስ ሲጠይቅዋት ከማንቀሳቀስ አልፋ ስሟን እንደነገረቻቸው፣ ሁለት ልጆችም አብረዋት እንዳሉ እንደነገረቻቸው ሮዶልፎ ሩቫልካቫ የተባለ የመድህን ሰራተኛ “ፎርቶ” ለተባለ የቴሌቪዥን ጣብያ ገልጿል።
ሌሎች አስከሬኖችም አሉ፣ በህይወት የተረፉ ሰዎች ካሉ አናውቅም ሲልም አክሏል።