Your browser doesn’t support HTML5
በምዕራብ ጎንደር አካባቢዎች በተቀሰቀሰው ግጭት ሳቢያ፣ በመተማ በኩል ያለው የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበር ዘመጋቱን የመተማ ዮሃንስ ከተማ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ ለአሜሪካ ድምፅ በኢሜይል ማብራሪያ የሰጠው የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር (ዩኤንኤችሲአር) በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች እና ባልታወቁ ታጣቂዎች መካከል ባለው ግጭት የተነሳ ኢትዮጵያን ከሱዳን የሚያገናኘው የጋላባት-መተማ ድንበር መዘጋቱን አስታውቋል፡፡
በአካባቢው በተካሄደው ግጭት በስደተኞች ላይ የደረሰ ጉዳት ግን አለመኖሩን ገልጸዋል፡፡ በመተማ ወረዳ የተለያዩ አካባቢዎች፣ በመንግስት የፀጥታ ሐይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭቶች መቀጠላቸውንም የአሜሪካ ድምፅ ምንጮች አመልክተዋል።