በሌላ የፍርድ ቤት ዜና የአቶ ዮናታን ተስፋዬ የይግባኝ ክርክር ተሰምቷል የአቶ ማሙሸት አማረ የክስ መቃወሚያ ደግሞ ውድቅ ተደረጓል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በቀድሞው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምሕርና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ ሊቀምንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ላይ ሁለት የዐቃቤ ሕግ የደረጃ ምስክሮች በዛሬ ዕለት ተሰሙ።
አንደኛው ምስክር ከኮምፒዩተራቸው ውስጥ 100 ገፅ ወረቀት ሲታተም ማየቱን ሲናገር አንደኛው ምስክር በበኩሉ 146 ገፅ መውረዱን ለችሎት አስረድቷል ሲሉ ከጠበቆቹ አንዱ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገርዋል።
ችሎቱን የተከታተሉ ሌሎች ሰዎችም በበኩላቸው ሁለቱ ምስክሮች በአንድ ላይ ነበርን ያሉበትን ጉዳይ በማይጣም መልኩ ምስክርነት ሰጥተዋል ሲሉ ሁኔታውን አስረድተዋል።
በሌላ በኩል በቀድሞው የሰማያዊው ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት የአቶ ዮናታን ተስፋዬ የይግባኝ ክርክር ተሰምቷል።
በሌላ የፍርድ ቤት ዜና የቀድሞው የመኢአድ አመራር አባል አቶ ማሙሸት አማረ የክስ መቃወሚያ ውድቅ ተደርጓል።
የጽዮን ግርማን ዝርዝር ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5